ሦስት ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሣኔ አንቀበልም አሉ

ቅዱስ ሲኖዶስ የጉባኤውን አባላት እንዲያጠራ ያሳሰብነው ለዚህ ነበር፡፡

የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ፓትርያሪክ ፈሪ ሲኖዶስ ነው እያልን ስናሳስብ ቆይተናል፡፡ አሁን ነገሮች ሁሉ በፍጥነት እየበረሩ ይገኛሉ፡፡ የጃዋር ክንፍ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማፈራረስ ያቀደው ዕቅድ ከፍ ብሎ ሥራውን ጀምሯል፡፡ የቀረው እውነታውን መጋፈጥ ብቻ ነው፡፡ ዘረኝነትን ከቤተ ክህነታችን ነቅለን እስካልጣልነው ድረስ ዕረፍት አይኖረንም፡፡

አቡነ ሳዊሮስን ፓትርያርክ አድርጎ በፖለቲካው ግለት እየከነፈ አዲስ ሀገር ለመመሥረት የሚሮጠው ቡድን ራሱን አጋልጧል፡፡ ከእንግዲህ የቀረው ነጭ ነጩን መነጋገር ብቻ ነው፡፡ በአቡነ ሳዊሮስ፣ አቡነ ዜና ማርቆስ እና አቡነ ሚካኤል የተመራው ጋዜጣዊ መግለጫ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሣኔ እንደማይቀበለው ዛሬ ድንቁ ደያስ የተባለው ባለሀብት ጨፌ ኦሮሚያ አጠገብ ፍላሚንጎ አካባቢ በሰጠው ቢሮ አሳውቋል ፡፡ (ቀደም ሲል በኦፌኮ ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫው መሰጠቱን ተናግረን የነበረ ሲኾን አሁን ቦታው ሌላ መኾኑን አረጋግጠናል፡፡)

አሁን በፍጥነት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን ለማየት ጉባኤ መጥራት ይገባዋል፡፡ ነገሮችን የሚያጣራ አስቸኳይ ልኡክ ሊሰይም ይገባል፡፡ የተሰበሰቡት አባቶች ምንም የሱባኤ መግቢያ ላይ ብንገኝም አጀንዳውን ክፍት አድርገው ለሚገባው አካል ኃላፊነቱን ሰጥተው ሊመለሱ ይገባል፡፡ ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በርጥቡ የሚባለው አሁንም ይሠራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *