የፓሪስ ምልክቶች ከሚባሉት አንዱ የሆነው የኖተርዳም ካቴድራልን ግማሽ አካል ያወደመው ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል

This image has an empty alt attribute; its file name is download-2.png

 የፓሪስ ምልክቶች ከሚባሉት አንዱ የሆነው የኖተርዳም ካቴድራልን ግማሽ አካል ያወደመው ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን የከተማይቱ የእሳት አደጋ ተከላካይ ብርጌድ ዛሬ ከሰዓት አስታውቋል። የእሳት አደጋ ተከላካዮች 850 ዓመት ዕድሜ ያለውን ካቴድራል ዋና የአለት መዋቅር የታደጉት ቢሆንም ጣሪያውን እና ሌሎች የቤተክርስቲያኑ ክፍሎች ግን በቃጠሎ ወድመዋል።

የካቴደራሉ ቃጠሎ በድንገተኛ አደጋ ሳይከሰት እንዳልቀረ የገለጹት የፈረንሳይ አቃቤ ህግ ሬሜ ሄይትዝ ሆን ተብሎ እሳቱ ተያይዞ እንደው የሚሳይ ምልክት እስካሁን አልተገኘም ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ ካቴድራሉን “መልስን እንገነባዋለን” ሲሉ ቃል ገብተዋል። የፈረንሳይ ቱጃር ቤተሰቦች እና ኮርፖሬሽኖች ለቤተክርስቲያኑ መልሶ ግንባታ እስካሁን 600 ሚሊዮን ዩሮ ቃል ገብተዋል። ከእዚህ ውስጥ 200 ዩሮ የሚሆነውን ከፍተኛ ገንዘብ ለመለገስ ቃሉን የሰጠው ዕውቁ የኮስሞቲክስ ኩባንያ ሎሬያል ነው።

( ሃይማኖት ጥሩነህ- ከፓሪስ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *