ጠ/ሚ አብይ ከጤና ባለሙያዎች ጋር ሊመክሩ ነው።

⬆️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች ጋር ሊወያዩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከጤና ባለሙያዎች ጋር የሚያደርጉት ውይይትም የፊታችን ቅዳሜ ሚያዝያ 26 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን አስታውቀዋል።

በጤና ባለሙያዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ላይ እንዳሉ የሚታወስ ሲሆን፥ ውይይቱም በጥያቄዎቹ ላይ እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *