ኦዴፓ ኢ/ር ታከለ ኡማ በሀላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ወሰነ

ሰበር መረጃ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው እንደሚነሱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል የደረሳቸው ቢሆንም በደረሰን መረጃ መሰረት ፓርቲያቸው ባሉበት ሀላፊነት እንዲቀጥሉ ወስኗል። በመሆኑም በገቢዎች ሚኒስትሯ ክብርት አዳነች አቤቤ ሊተኩ ነው የተባለውን ዜና የከንቲባው ኦፊሽያል የፌስቡክ ገጽ አስተባብሏል። አዴፓ በተደጋጋሚ አባሎቹ ከአዲስ አበባ መዋቅር እየተገለሉ ነው በማለት ቅሬታ ሲያቀርብ ቆይቷል። ኦዴፓም በግምገማው አዲስ አበባ ውስጥ ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን መያዙን አምኗል።
በአክራሪዎችና በለዘብተኛ ብሄርተኞች ፉክክር ውስጥ የወደቀ ኦዴፓ ለቀናት በፊት ኢ/ር ታከለን ከስልጣን እንዲነሱ ወስኖባቸው ነበር። በሚሰሯቸው ስራዎች ብዙዎች ቅሬታ ቢያነሱባቸውም እሳቸውን የሚደግፍ ክፍል መኖሩን በአደባባይ የሚታይ ሀቅ ነው። ለምክትል ከንቲባው ከስልጣን መነሳት እንደምክንያት የቀረበው የባለደራው ምክር ቤት ሊያደርገው ያቀደውን ሰላማዊ ሰልፍ መስተዳድሩ ቢፈቅድም በኦሮሚያ ፖሊስ በመከልከሉ ምክንያት እንደሆነ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸውልናል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በኦዴፓ ውስጥ በጃዋር የሚደገፈው እና በአቶ ታየ ደንድአ ና ዶ/ር ሚልኬሳ ቡድን ና በእነ ኢ/ር ታከለ ቡድን መካከል ከፍተኛ የስልጣን ሽኩቻ መኖሩም ተገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሀላፊነት ቦታቸው ሊነሱ የነበሩት ምክትል ከንቲባው በስራቸው ይቀጥላሉ ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *