ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቁጥጥር ስር ውሏል

ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በቁጥጥር ስር ውሏል(የገቢዎች ሚኒስቴር፣ ሚያዝያ 29/2011 ዓ.ም)
በያዝነው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ በድምሩ 37,488,463.1 ብር የሚገመት ማዕድናት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በገቢ ኮንትሮባንድ 19,445,983.10 ብር እና በወጪ ኮንትሮባንድ 18,042,480 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ማዕድናት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡በቁጥጥር ስር ከዋሉት ማዕድናት መካከል 19,166,863.1 ብር የሚገመተው ብር፣ 11,321,600 ብር የሚገመተው ሌሎች ማዕድናት እና 7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ወርቅ ናቸው፡፡
ሀገራችን ከወርቅ የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ በኮንትሮባድ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መቀነሱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡ ሀገራችን ከአምስት ዓመታት በፊት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከወርቅ ስታገኝ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከወርቅ የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ እንደሆነ ተገልፆአል፡፡

ምንጭ፡ የገቢዎች ሚኒስቴር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *