የ አለማችን ትልቁን ተራራ ኤቨረስትን በመውጣት ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ሲራክ ስዩም

ነዋሪነቱን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ያደረገውና የኤሌክትሪካል ምህንድስና ባለሙያው ሲራክ ስዩም ከበርካታ ልምምድ በኋላ የዓለማችን ትልቁን ተራራ፣ ኤቨረስትን ዛሬ መውጣት እንደሚጀምር ገለፀ። ሲራክ እንደሚለዉ ተራራዉን በመዉጣት ብቸኛዉ ኢትዮጵያዊ መሆኑንም አክሎ ገልጿል

“የኔፓል የቱሪዝም ኮሚሽን ማን ተራራ እንደወጣ፣ ማን እንደሞከረ፣ ማን ድጋሜ እንደወጣ የሚመዘግቡበት መዝገብ አላቸው፤ መዝገቡ ከአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 1937 ጀምሮ የወጡ ሰዎች ስም ዝርዝር ሰፍሮበታል፤ በመሆኑም እስካሁን ብቸኛው ኢትዮጵያዊ እንደሆንኩ ነው የማውቀው” ሲል የመጀመሪያው ስለመሆኑ ያስረዳል፡፡

Image result for sirak seyoum everest mountain

በርካቶች ሲያዩትም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ፎቶ ለመነሳት ይሽቀዳደማሉ ብሎናል።ተራራ መውጣት የረዥም ጊዜ ህልሙ የነበረ ሲሆን፤ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ይህንኑ ተራራ ለመውጣት እቅድ እንደያዘ አሳውቆ ነበር፡፡

አንድም በቂ ልምምድ ማድረግ እንዳለበት ልምድ ካላቸው ሰዎች ስለተነገረው፤ ሁለትም ያለው የገንዘብ አቅም ወጭውን የሚሸፍን ሆኖ ስላላገኘው፤ በሌላም በኩል በአባቱ ሕልፈት ምክንያት ከባድ ሃዘን ውስጥ ስለነበር ህልሙን ሳያሳካው ቆይቷል፡፡

” በጣም ደስ የሚል መጽሐፍ አንብበን ስንጨርስ፤ ሌላ ማንበብ እንደሚያሰኘን ሁሉ፤ ተራራ መውጣትም እንደዚያው ነው” የሚለው ሲራክ፤ በኢኳዶር የሚገኘውን ቺምፖራዞን ተራራ ከወጣ በኋላ ተራራ የመውጣት ፍቅር እንዳደረበት ይናገራል፡፡

ምንጭ፣ቢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *