ቻይና እ.አ.አ 2018 ድረስ የተጠራቀመውን የኢትዮጵያን የብድር ወለድ ሰረዘች::

ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር ከቤልት ኤንድ ሮድ ጉባኤ በፊት የሁለትዮሽ ውይይት አካሄዱ::

በውይይቱ ወቅትም ፕሬዝዳንቱ እስከ የፈረንጆች 2018 ዓ.ም መጨረሻ የተጠራቀመ የብድር ወለድን ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘ አስታውቀዋል

የጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ አሕመድን አመራርና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ የገለጹት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ ቻይና ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ብለዋል::

ከዚሁም ጋር የቻይና መንግሥት የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክትን ጠቀሜታ ይረዳል ያሉት ፕሬዝዳንት ዥንፒንግ ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል::

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገለጻ ሁለቱም ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን ትብብር በተለያዩ ዘርፎች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል::

ምንጭ፡-ኢ.ፕ.ድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *