ቃር ያስቸግሮታል

የቃር (Heart burn) እና የልብ ድካም (Heart Attack) ምልክቶች በቀላሉ ያደናግራሉ፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በደረት ላይ የሚከሰት የማቃጠል ስሜት የሚፈጥሩ በመሆኑ ነው፡፡ቃር (Heart burn) በዋናነት በጨጓራ ውስጥ ምግብ ለመፍጨት (ለማላም) የሚጠቅመን አሲድ ወደ ምግብ መውረጃ ቧንቧ (Esophagus) በመርጨት የሚከሰት ነው፡፡

ምግብ በምንመገብበት ጊዜ የምግብ መውረጃ ቧንቧ ከጨጓራችን ጋር በሚገናኙበት አንጓ ላይ የሚገኙ ጡንቻዎች በሚፈታቱበት (Relax) ጊዜ ምግብ የሚፈጨው አሲድ ወደ ምግብ መውረጃ ቧንቧ የመመለስ ውጤት ነው፡፡ቃር በራሱ በሽታ ሳይሆን የአሲድ ጋስትሪክ ሪፍሌክስ በሽታ (Acid Gastric Reflux Disease) ምልክት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ቃር የሚከሰተው ምግብ ከተመገብ በኃላ ወዲያው ጋደም ስንል ወይም አጎንብሰን ስራዎችን ስናከናውን ነው፡፡በተለይ በምሽት ቃር ብዙዎች የሚያስቸግራቸው ሲሆን አፋቸውንም መራራ ስሜቶች ሊሰማቸው ይችላል፡፡
ቃር በተደጋጋሚ ሲከሰት የምግብ መውረጃ ቧንቧ (Esophagus) በማቁሰል የሚየደማ ሲሆን እየባሰ ከሄደ ደግሞ ይሄው አካል በካንሰር ሊጠቃ ይችላል፡፡ በዚህም የተነሳ መግብ ለመዋጥ ከመቸገር አንስቶ ለሞት ይዳርጋል፡፡

ቃርን የሚያባብሱ ምግቦ ችአልኮል፣ ካፊን ያለባቸው መጠጦች( ቡና፣ሻይ፣ኮካ የመሳሰሉት)፣አስፕሪን፣ካርቦኔትድ መጠጦች፣ በውስጣቸው አሲድ ያለባቸው የፍራፍሬ ጭማቂዎች( የወይን፣ የብርቱካንና የአናናስ)፣አሲድነት ያላቸው ምግቦች (ቲማቲም)፣ ቸኮሌት፣ ሲጋራ ማጨስ ፣ እርግዝናና ከመጠን ያለፈ ክብደት ተጠቃሽ ምክንያቶች ናቸው፡፡

መፍትሔውስ

1.ያለ ሐኪም ማዘዣ የሚሸጡ ጸረ- አሲድ መድኃኒቶችን መጠቀም
2. ምግብ ከተመገብን በኃላ ወዲያውኑ አለመተኛት
3. በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚታዘዘውን Nexum የተሰኘ መድኃኒት መውሰድ ችግሩን በስፋት ያቃልላል፡፡
4. የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ለማየት የኢንዶስኮፒ ምርመራ ማካሄድ፡፡

ምንጭ፡ ጌጡ ተመስገን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *