ዓረና የመንግሥት የፀጥታ አካላትን ከሰሰ

በመቀሌ ከተማ ኲሓ ክፍለከተማ ኲሓ በትናንትናው ዕለት በነበረው የፅዳት ዘመቻ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በአባላቶቼና በሌሎች ወጣቶች አካላዊ ጥቃት ተፈፅምዋል እንዲሁም ታሰሩ ሲል የዓረና ትግራይ ፓርቲ ከሰሰ።መቀሌ — 

የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ እንደገለፁት እነዚህ ወገኖች ያሉበት ሁኔታ ለማየት የት እንዳሉ ለማወቅ አልቻልንም ሲሉ ተናገሩ።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ገብረክርስቶስ ገብረመስቀል የታሰሩት ሰዎች የአካባቢው ሰላም ለማወክ ስለተንቀሳቀሱና የፖሊሰ አባላትም ስለመቱ ነው በቁጥጥር ሥር ያዋልናቸው ብለዋል።

በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎችም በክፍለ ከተማው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *