የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጽህፈት ቤት በሶስቱ የመንግስት አካላት ግንኙነት እና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አተገባበር ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።ምክር ቤቱ በህግ አውጪ፣ በህግ ተርጓሚ እና በህግ አስፈጻሚ አካላት መካከል ባለው ግንኙነት፣ ቁጥጥር፣ አተገባበር እንዲሁም በዲሞክራሲ ግንባታው ዙሪያ በሚታዩ ተስፋዎች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ ነው እየመከረ የሚገኘው።

የምክክር መድረኩ ዓላማ ሶስቱም አካላት በተሰጣቸው ህገ መንግስታዊ ስልጣን መሰረት ስራቸውን ለመስራት እያደረጉት ያለውን ጥረት በመገምገም ፣ ወደ ፊት እንዴት ውጤታማ መሆን እንዳለባቸው የሚጠቁም መሆኑን የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ አመላክተዋል።”ቤት ሲሰራ ግድግዳ፣ማገር እና ጣሪያ እንደሚያስፈልጉ ሁሉ ህግ አውጪው ፣ ህግ ተርጓሚው እና ህግ አስፈጻሚው በአንድነት ተናበው መስራት አለባቸዉ ” ብለዋል። የክልሉን ሕዝብ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበትም አፈ ጉባኤዋ አስረድተዋል።

ዘጋቢ፦ ኃይሉ ማሞ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *