⬆️ በተለያዩ ከተሞች የሚስተዋለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ህገወጥ ምንዛሬ።

⬆️
በተለያዩ ከተሞች የሚስተዋለው የውጭ ሀገራት ገንዘብ ህገወጥ ምንዛሬ በትላልቅ አስመጪዎች እና በባንክ ማናጀሮች ዋነኛ ተዋናይነት የሚመራ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገለጸ።

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስ ወንጀሎች ምርመራ ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ የውጭ አገራት ገንዘብ ምንዛሬ ዋነኛ ተዋናዮች አስመጪዎች፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች በተለይም የባንክ ማናጀሮች ናቸው። በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ግን ሶስተኛ ወይንም አራተኛ አካላት ናቸው።

እንደ ኮማንደር ታደሰ ገለጻ፣ በየአካባቢው የሚገኙት ዶላር መንዛሬዎች ዋነኛ የህገወጥ ተግባሩ ተዋናዮችን በውል የማያውቁ እና ለእነርሱ የሚሰሩ ናቸው። ህገወጥ ተግባሩ በተዋረድ (በኔትወርክ) የሚከናወን እና በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ያላቸው አስመጪዎች የሚያንቀሳቅሱት ነው።

በተጨማሪ የባንክ ማናጀሮች ዶላር ፈልጎ የመጣን ባለሀብት ቢሮክራሲ በማብዛት ዶላር እንደሌለ አስመስለው ያባርራሉ። በጎን ደግሞ ደላሎችን ልከው ወደ ህገወጥ መንገድ እንዲሄዱ በማመቻቸት ገንዘብ ተቀብለው ይሰጧቸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *