የቦሌ ሚካኤሉ ግጭት

ከምሽቱ 2ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ የቦሌ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች የፈጠሩት ቄሮ የተባለው አጽራረ ቤተክርስቲያን መንጋ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ሰንዝሯል። ከአርሲ፣ከሀረርጌ እና ከባሌ ተወጣጥቶ በአዲስ አበባ ዙሪያ እንዲሰፍር የተደረገው ጽንፈኛው እና አክራሪው ቄሮ ወደ ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ በመግባት የኢትዮጵያን ባንዲራ ለማውረድ እና ቤተክርስቲያን ለማቃጠል ሲሞክር በአቅራቢያው ከነበረው ምዕመናን እና የአካባቢው ሰው ጋር ተላትሟል። ቄሮ ይህን ቤተክርስሪታን ለማቃጠል ሲሞክር ሁለተኛ ጊዜው ሲሆን ዛሬም እንደትናንቱ በከፍተኛ የህዝብ ርብርብ ያሳቡትን ሳያሳኩ ቀርተዋል።

ይሁን እንጅ በዚህ እልህ አስጨራሽ ግብግብ ውስጥ ቁጥራቸው 20 የሚደርሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች ታርጋ ቁጥር 0101 የሆነ አ/አ ፖሊስ እና ታርጋ በሌለው የፌደራል ፒክ አፕ መኪኖች ወደቦታው ደርሰው ወዲያውኑ ቤተ ክርስቲያኑን ለመታደግ በተሰበሰበው ምዕመናን ላይ ዱላቸውን ማውረድ ጀመሩ። ይህ ሲሆን እኔ(የመረጃው ምንጭ) በእውነት የማየውን ማመን አቃተኝ። ቤተክርስቲያን ለማቃጠል የሚሞክሩትን ቄሮዎች ይዘው ለፍትህ ያቀርባሉ የተባሉት ፖሊሶች በህዝቡ ላይ ተጨማሪ ዱላ አወረዱበት። ህዝቡም ከሁለት አቅጣጫ የሚወርድበትን ዱላ በጋራ ሆኖ በቆራጥነት መከተ። ህዝቡ ቤተክርስቲያኑን እና ራሱን ሞት ሳይፈራ ተከላከለ። ፖሊስም ህዝቡ ቄሮ ከአካባቢው ሳይርቅ ለማንም እንደማይመለስ ሲረዳ ወደ ሰላማዊው ህዝብ ጥይት መተኮስ ጀመረ።

በዚህም አራት ኦርቶዶክሳዊያንን መትቶ ጣለ። እስካሁን አንድ ሰው መሞቱ ተረጋግጧል። ሁለቱ በካባድ ቆስለዋል። አንዱ ያለበት ሁኔታ በግልጽ ባይታወቅም የታርጋ ቁጥሩ 0057 በሆነ የፖሊስ መኪና ተጭኖ ተወስዷል። ከደረቱ ላይ ከፍተኛ ደም እየፈሰሰ እንደነበር እና በእድሚያቸው ጠና ያሉ ሰው እንደሆኑም በስፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። እግዚአብሄር የሞተውን ወንድማችንን ነፍስ ይማር፣ የቆሰሉትንም በቶሎ እንዲያገግሙ ያድርግልን። አሜን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *