2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መገኘቱ ተገለጸ


ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ፍላጎት አሳይተው ከተመለመሉ የውጭ ባለሀብቶች ውስጥ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መገኘቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ባለሀብቶችን በመመልመልና በመሳብ ረገድ አመርቂ ሥራ ተሠርቷል፡፡ እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ተችሏል፡፡
አፈፃፀሙ ሲታይ 70 በመቶ ሲሆን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 40 በመቶ ዕድገት አስመ ዝግቧል ብለዋል፡፡ በዘርፉ የተመዘገው አመርቂ ውጤት የተገኘው አንድ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያስመዘገበውን የኢግል ሂልስ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጨምሮ 225 ፕሮጀክቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ እንዲያወጡና ወደ ሥራ እንዲገቡ በመደረጉ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡ ኢ.ፕ.ድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *