የሲዳማ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ በሆነው ኤጄቶ ላይ የተቃጣው ፍረጃና ዛቻ ሊቆም ይገባል፦ የሲዳማ ዞን አስተዳደር

የሲዳማ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በሆኑት ኤጄቶዎች ላይ የተቃጣው የፍረጃ፣ ዛቻና ድብደባ ጥቃት በአስቸኳይ ልቆም ይገባል ሲል የሲዳማ ዞን አስተዳደር አሳሰበ።አስተዳደሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ኤጄቶ ለውጡን የሚፃረርና የሚቃወም እንደሆነ ተደርጎ በጥቂት ግለሰቦችና ሚዲያዎች የሚገለፀው ተገቢነት የሌለው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ኤጄቶ ተራማጅ አመለካከት ያለው የትግልና ለውጥ ተምሳሌት የሆነ የሰላም ሀይል ነው ያለው አስተዳደሩ ይህንን እውነታ መካድ ኑፋቄ ይሆናል ሲልም ገልጿል።

በግንቦት ወር መጨረሻ የሚከበረው የሲዳማ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫንባላላ በዓል ገፅታን ለማጠልሸት እነዚህ አካላት ከወዲሁ ያልሆነውን ሆነ፤ ያልተፈፀመውን ተፈፀመ በማለት የውሸት መረጃ እያሰራጩ ይገኛል ብሏል።ይሄ እኩይ ምግባራቸው በህዝቦች መካከል ቅራኔ እና ግጭትን ከመዝራት ባለፈ ምንም ፈይዳ የሌለው መሆኑን በመረዳት ከተግባራችው ሊታቀቡ እንደሚገባ አስታውቋል፡፡UNESCO ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች ተርታ የመዘገበው ፍቼ ጫንባላላ በዓል የሲዳማ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ክብር በመሆኑ አለአግባብ ይህንን በዓል ለማጠልሸት መሞከር የሀገርን ክብር መንካት እንደሆነ አስተዳደሩ አፅንኦት ሰጥቶ ገልጿል፡፡

ምንጭ፡ ጋሞ ሜዲያ ኔትወርክ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *