በሩሲያ በአውሮፕላን አደጋ 41 ሰዎች ሞቱ

ከሩሲያ ሞስኮ የተነሳ ኤሮፍሎት ጄት በድንገት መልሶ እንዲያርፍ ሲሞክር እሳት በመነሳቱ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል፤ በአደጋውም የ41 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡በሕይወት የተረፉ መንገደኞች አውሮፕላኑ በመብረቅ መመታቱን ተናገርዋል፤ የሩሲያ ብሔራዊ አየር መንገድ ግን በቴክኒክ ችግር አደጋው መድረሱን አስታውቋል፡፡

አውሮፕላኑ 73 መንገደኞችንና አምስት የበረራ ቡድን አባላትን ይዞ ነበር፡፡አንዳንዶች አውሮፕላኑ እየነደደ ማረፉን ሲናገሩ አንዳንዶች ደግሞ በድንገት ያረፈበት መንገድ ቃጠሎ ማስነሳቱን እየተናሩ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

በአብርሃም በዕውቀት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *