አፋር እና ሶማሌ።

⬆️
ከአ.ህ.ፓ የተሰጠ መግለጫ

ሳይቃጠል በቅጠል

የአፋር እና የኢሳ-ሶማሌ ጦርነት የረጂም ጊዜ ታሪክ ያለው እና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥናት ከተደረገባቸው ግጭቶች መካከል እንዱ እና ቀዳሚ ስፈራ የሚዝ ነው፡፡ ግጭቱ ጣልያን አገራችን በድጋሚ ከወረረበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 60 ዓመታት የተለያየ መልክ እና ገጽታ በመያዚያ እነሆ አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል፡፡ አገራችንን ላላፉት 50 ዓመታ የመሩ መንግስታት እና አገዛዞችም ለግጭቱ ዘላቂ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ ለየ ስርዓቶቻቸው የፖለቲካ ሴራ መስፈጸሚያ በማድረግ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲጠቀሙበት ቆይተዋል፡፡ የግጭቱን ታሪካዊ ዳራ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንመለከት የአፋር እና ኢሳ ግጭት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ጣልያን አገራችን ወሮ በሃይል መግዛት በጀመረ ማግስት በድሬደዋ እና አከባቢዋ የቀኝ አገዛዙን ለማስፈን የአገሬውን ሰው ድጋፍ እና ትብብር በፈለገ ጊዜ መሆኑ ይታመናል፡፡በወቅቱ በድሬደዋ ይኖሩ የነበሩት የአፋር ማህበረሰቦች ወራሪውን የጣሊያን አገዛዝ ለመተባበር አሻፈረኝ በማለታቸው የበቀል በሚመስል መልኩ የጣሊያኑ ወራሪ በወቅቱ አይሻ በሚባል ቦታ ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ የኢሳ ማህበረሰብ አባላትን ወደ ድሬደዋ አምጥቶ መሳሪያ አሰታጥቆ የአከባቢውን ፀጥታ አስከባሪ በሚል ያደራጃቸዋል፡፡ በወቅቱም በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል በተዳጋገሚ አለመግባበቶች ሲፈጠሩ ከቆዩ በኋላ ወደ ለይለት ግጭት አመሩ፡፡ ወራሪው ፋሺስታዊ የጣሊያን አገዛዝም በአገራችን አርበኞች ትግል እና በወቅቱ አገራችንን ትደግፍ በነበረችው ወዳጅ አገር ታላቋ ብሪታኒያ ድጋፍ ተሸንፎ ወደ አገሩ ሲመለስ በቀኝ አገዛዙ ወቅት የአገዛዙ አስፈጻሚ ለነበሩት እና በሚሊሻ መልክ ላደረጃቸው የኢሳ ማህበረስ አባላት የጦር መሳሪያውን ትቶ ይሄዳል፡፡ ወራሪው የጣልያን ጦር ከአገር ከወጣ ጊዜ ጀመሩ ዘመናዊ መሰሪያ የታጠቀው የኢሳ ማህበረሰብ የመሳሪያ የበላይነቱን በመጠቀም በአካባቢው ለዘመናት የኖረውን የአፋር ማህበረሰብን ከቀያው ማፈናቀል ይጀምራል፡፡ በሁለቱ ማህበረስብ መካከል በጣልያን ወረራ ማግስት የጀመረው ጦርነት በላፉት ሶስት መንግስታት ወቅት በተለያዩ ጊዜት የተደረጉ ስምምነቶች መፍትሄ ሳይሰጡት እነሆ ይህ ያላቁረጠው ጦርንት አሁን ላለበት ደረጃ ደርሶል፡፡ የቅርብ ጊዜያት ክስተቶችን ስንመለከት ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ እና ሲያጠኑ የነበሩ የዘረፉ ባለሞያዎችን ድምዳሜ ውድቅ በሚያደርግ መልኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያለው ግጭት ከአኗኗር ዘይቢያቸው የመንጨ እና የውሃ እና ግጦሽ ግጭት እንዳልሆነ የኢሳ ማህበረሰብ ባላፉት 5 አስርት ዓመታት እያደረገ ካለው የግዛት ማስፋፈት መረዳት ይቻላል፡፡
የአፋር ማህበረስብ ለሰላም ካለው ጽኑ ፍላጎት በመነሳት በላፉት ሶስት ስርዓታት የተደረጉ የተለያዩ ስምምነቶችን በማክበር በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ያለወን ቁረጠኝነት አሳይቶል፡፡ በተቃራኒው የኢሳ ማህበረሰብ ሲፈልግ አገርን ቀኝ ለመግዛት ከመጣ ጠላት ጋር በመተባበር በሌላ ጊዜም የአገራችን አንድነት ለማፈረስ እና ታላቋን ሶማሊያ ለመመስረት ቆርጠው ከተነሱ የአገር ጠላቶች ጋር በማበር ግዛቱን በሃይል የማስፋፋት እርምጃውን ቀጥሎበታል፡፡ የአፋር ህዝብ ይሄን ሁሉ ግፍ ችሎ እና ለዘመናት ህልውናውን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሰውን ጠላት መመለስ እና እራሱን መከላከል አቅቶት ሳይሆን ቻይ እና ሆደ-ሰፊ በማሆን በሁለቱ ማህረሰብ ማካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ካለው ጽኑ ፍላጎት ነው፡፡ ለዚሁ ፋለጎቱ ማሳያ የሚሆነው በዘመናዊ የጦር መሰራያ ሃይልና በኮትሮባንዲስቶች በሚታገዘው ወራሪው የኢሳ ሃይል በጉልበት የተነጠቁትን እና በአፋር ክልል እምብረት የሚገኙ 3 የአፋር ከተሞች (አዳይቱ፣ኡንዳፎኦ እና ገዳማይቱ) የኢሳ ልዩ ቀበሌ ተብለው ህዝቡን በማይወክሉ የጊዜው አሰተዳደሮች ሲወሰን ስምምነቱን ሳይቀበል ለጊዜው በዝምታ ያለፈው፡፡ ይህ ዝምታና ሰላም ፈላጊነቱ ግን ከወረራና ግድያ ሊያጥለው ባልመቻሉ በቀዬው ከመሞት በስተቀር ሌላ አማራጭ አልተገኘለትም።

ስለሆነም የአፋር ህዝብ ፓርቲ የሶማሊ ክልላዊ መንግስት ካቤኔ በዛሬው እለት ባደረገው አስቸኮይ ስብሰባ የወሰነው ውሳኔ ሃገራዊ ሃላፊነት የጎደልው ብቻ ሳይሆ ችግሩን አርግቦ ለሰላም ከመስራት ይልቅ በእብሪተኝነት የትሞላና ጠብ አጫሪ በመሆኑ፣ የሚከተለውን የአቋም መገለጫ አውጥቷል፡፡

  1. የሶማሌ ክልላዊ መንግስት በ2007 ዓ.ል በሁለቱ ክልሎች መካከል የተደረገውን ስምምነት ውድቅ በማድረግ የሶማሌ ክልል የልዩ ሃይል አባለት ወደ ሶስቱ ከተሞች ለማሰማራት የወሰነው ውስኔ ሁለቱን ክልሎች ወደ ለየለት ግጭት ሊያመራ የሚችል በመሆኑ የአፋር ህዘብ ፓርቲ መግለጫዉን በጽኑ ያወግዘዋል፡፡ ለሁላችንም የሚበጀው ሰላምና የህግ የበላይንትን ማስከበር ስለሆነ፣ የሶማሌ ክልል ለመልካም ጉርብትናና ለአብሮነት ቅድሚያ እንዲሰጥ እናሳስባለን።
  2. የሶማሌ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት ያስተላለፈው ውሳኔ በአፋር እና ኢሳ ማህበረሰብ ማካከል ከላፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ የተከሰተውን ግጭት የሚያባብስ እና አከባቢውን ወደ ከባድ ቀውስ የሚመራ በመሆኑ የሶማሌ ክልላዊ መንግስ ወሳኔው እንደገና እንዲያጤን የኢ.ህ.ፓ በጽኑ ያሳስባል፡፡
  3. የፌደራሉ መንግስት ውሳኔውን ተከትሎ በሁለቱ ክልሎች መካከል ሊፈጠር የሚችለውን ግጭት ከወዲሁ ለማስቀረት አስቸኮይ መፍትሄ እንዲሻ እናሳስባለን፡፡
  4. በተደጋጋሚ እንደገልጽነው በሁለቱ ክልሎች መካከል በ2007 የተደርገውና አሁን የሶማሊ ክልል ካቢኔ ውድቅ አድርጌዋለሁ የሚለውን የወሰን ማካለል ሰራ በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆል እናሳስባለን።
  5. በመጨረሻም በሁለቱ ክልሎችና ህዝቦች መካከል የዕርቀሰላም ጉባኤ እንዲደረግና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዲጎለብት የፌደራል መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ እናሳስባለን።

ሚያዚያ 26/2011

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *