ፖሊስ የአዲስ አበባ ባለ-አደራ ደጋፊዎች የተለያዩ የከተማው ቦታዎች የሰቀሉትን ባነሮች ከደንብ አስከባሪዎች ጋር በመሆን እያወረደ መሆኑ ታውቋል። በሌላ ዜና በዶሮ ማነቂያ አካባቢ በስራ ላይ የሚገኙ ሁለት ግለሰቦችን ባነር የሰቀላችሁት እናተ ናችሁ በማለት በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ባነሩ የተሰቀለበት ፖል አጠገብ የግሮሰሪ ባለቤት የሆኑት አቶ ሲሳይ የተባለ ግለሰብ እና በአካባቢው ላይ በልብስ ስፌት የሚተዳደር አቶ ደምስ የተባለ ግለሰቦች በፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፎቶ: አቶ ሲሳይ በጣይቱ ፖሊስ ጣቢያ