መረጃ ለማካፈል ያክል

ባህርዳር ላይ ችግር በተፈጠረበት ዕለት፣ ጠሚኒስትር አብይ አህመድ ለአማራ ቲቪ የሰጡት መግለጫ ቀረጻ የተካሄደው ባህርዳር ላይ እንደነበር ተደርጎ የሚሰጡ አስታየቶችን አንብቤአለሁ። አንዳንድ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእለቱ ባህርዳር እንደነበሩ ለማሳየት እንደአንድ ማስረጃ ሲያቀርቡትም አያለሁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “በዕለቱ ባህርዳር ነበሩ ወይስ አልነበሩም” የሚለውን ለማወቅ ተጨማሪ ማጣራት ማድረግ የሚገባ ቢሆንም፣ ቀረጻው ባህርዳር ላይ እንደተካሄደ ተደርጎ የሚሰጠው አስተያየት ግን ትክክል አለመሆኑን ተረድቻለሁ። ቀረጻው የተካሄደው አዲስ አበባ ቤተመንግስት ውስጥ ነው። ጥሪው ለሁሉም የመንግስት ጋዜጠኞች ተልኮ ነበር። የአዲስ አበባ የአማራ ቲቪ ወኪል ጋዜጠኛ ጋሻው ፋንታሁን፣ ከሁሉም ቀድሞ በመድረስ ቀረጻውን ከምሽቱ 5 ሰዓት ከ45 ደቂቃ ላይ አካሂዷል። እሰከዚህ ሰዓት ድረስ ሌሎች ጋዜጠኞች አልደረሱም ነበር። ጋሻው ቀረጻውን አካሂዶ ሲጨረስ፣ መግለጫውን ወደ አማራ ቲቪ ለመላክ ቢሞክርም፣ ኢንተርኔት አልነበረም። ታክሲ ተክራይቶ ወደ ኢቲቪ በመሂድ ቪዲዮውን ከሰጣቸው በሁዋላ በሁሉም ሚዲያዎች እንዲተላለፍ ተደርጓል። ጋሻውም ራሱ ኢንተርኔት ሲለቀቅ የሚናገረው ነገር ሊሆን ይችላል። ዘግይተው የደረሱት ሌሎች ጋዜጠኞች፣ ከአማራ ቲቪ ውሰዱ ተብለው ቤተመንግስት ሳይገቡ ተመልሰዋል ።

Fasil Yenealem

Leave A Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *