የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ ከሕዝብ ጋር ይመክራሉ

የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጎንደር ከተማ ከሕዝብ ጋር ይመክራሉ።

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 24/2011ዓ.ም (አብመድ) በዶክተር አምባቸው መኮንን የሚመራው ቡድን ከጎንደር ፣ ከማዕከላዊ ጎንደር ፣ ከምዕራብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር ዞኖች እንዲሁም ከሦስቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ከአንድ ሺህ በላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ነው የሚመክረው።

ምክክሩ በጎንደር ከተማ አስተዳደር የዞኑ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አዳራሸ ይከናወናል።

ምክክሩ የጎንደር ሕዝብ የሚጠይቀውን ሁለንተናዊ ጥያቄ መንግሥት በግብዓትነት ወስዶ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ዕቅድ እንዲመልስ መነሻ ይሆነዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ውይይቱን እየተከታተለ የሚነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ያደርሳል።

መድረኩ በሌሎች ጉዳዮችም እስከ ነገ የሚቆይ እንደሆነ ከአስተባባሪ ኮሜቴዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ዘጋቢ :- ግርማ ተጫነ – ከጎንደር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *