የአዲስ አበባ ሰፈር ስሞች።

ዶሮ_ማነቂያ፦

ይህ ሰፈር በድሮ ጊዜ ወንጀለኞች በስቅላት ይቀጡበት የነበረ ዛፍ ይገኝበት ነበር።በጊዜ ብዛት ቦታው ላይ የስቅላት ቅጣት መፈጸም ቀረ፣ ስዎችም ሰፈሩን ' ድሮ ማነቂያ' እያሉ ይጠሩት ጀመር።በጊዜ ብዛት ድሮ ማነቂያ ወደ ዶሮ ማነቂያ ተለውጦ ቋሚ መጠሪያው ሆነ።

በቅሎ_ቤት፦

በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት መድፈኛ ጦር መቀመጫው ላንቻ አካባቢ የነበረ ሲሆን በወቅቱ መድፎችን ወደ ሌላ ቦታ መውሰድ ሲፈለግ ተፈታተው በበቅሎ ይጫኑ ነበር።በዚህ ምክንያት በመድፈኛ ጦር ሰፈር ውስጥ ለማጓጓዣነት የሚጠቅሙ ከመቶ ያላነሱ በቅሎዎች ነበሩ።በአካባቢው በርካታ በቅሎዎች ስለነበሩ ሰፈሩ “በቅሎ ሰፈር” እየቆየ ሲሄድ ደሞ “በቅሎ ቤት” እየተባለ መጠራት ጀመረ።

ሠራተኛ_ሰፈር፦

በአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ውስጥ በዕደ-ጥበባት ሙያ በተሰማሩ ሰራተኞች በመመስረቱ ሰራተኛ ሰፈር ተብሏል።

ሰባራ_ባቡር፦

ይህ ሰፈር ስያሜውን ያገኘው ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን በተባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ ሀገር መጥቶ አሁን ስያሜውን ባገኘበት ቦታ ተበላሽቶ በቀረው የመንገድ መስሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ነው።

አራት_ኪሎ፦

ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው አራት መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ ስለነበረ ነው።

ተረት_ሰፈር፦

  ተረት ሰፈር ስያሜውን ያገኘው በአዲስ አበባ ከተከፈቱት የመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች አንዱ በነበረው ሆቴል ዳፍራንስ ባለቤት በሆኑት ፈረንሳያዊ ሙሴ ቴረስ ስም ነው።

ጎፋ_ሰፈር፦

 በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን ለማይጨው ጦርነት ከጋሞ ጎፋ አከባቢ ለመጡና በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ትግል ላደረጉ አርበኞች የተሰጠ ቦታ በመሆኑ መጠሪያው ጎፋ ሰፈር ተብሏል።

ጠመንጃ_ያዥ፦

  ሰፈሩ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ይገኛል።ጠመንጃ ያዥ የተባለበት ምክንያት ከጣልያን ወረራ በፊት የቤተ መንግስት ጠባቂዎች በብዛት ይኖሩበት ስለነበረ ነው።

ፖፖላሬ፦

   በጣልያን ወረራ ወቅት ተራው ጣልያናዊ ሰራተኛ የሰፈረበት ሰፈር ነበር።ስያሜው ፖፖሎ ከሚለውና ሕዝብ የሚል ትርጉም ካለው የጣልያን ቃል የተወሰደ ነው።

ሸጎሌ-

  ሼህ ሆጀሌ የቤንሻንጉል ጉሙዝን አካባቢ ሲያስተዳድሩ የነበሩ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጅ ነበሩ።እኝህ ሰው ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ለማዕከላዊው መንግስት ታማኝ ሆነው አካባቢውን ከጠላት ወረራ ሲከላከሉ ኖረዋል።በዚህም የተነሳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሸጎሌ የሚባለው አካባቢ ቤተ-መንግስት አላቸው።በዚህም ምክንያት ሰፈሩ በስማቸው ሼህ ኦጀሌ ተባለ፤ በጊዜ ብዛትም ወደ ሸጎሌ ሊለወጥ ችሏል።


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *