ከ 2 ነጥብ 26 ሚሊዮን ብር

ከ2 ነጥብ 26 ሚሊዮን ብር በላይ ኮንትሮባንድ የግንባታና የኢንዱስትሪ ግብዓት በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ግምታዊ ዋጋው 1 ነጥብ 26 ሚሊዮን ብር የሆነ 8 ሺህ 401 ኪ.ግ አልሙኒዬም እና መዳብ መሰል የተቆራረጠ ሽቦ ከመሀል ሀገር ወደ ሞያሌ መስመር ሲሚንቶ ጭኖ ሲጓጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ የኮንትሮባንድ ዕቃውን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞከር በያቤሎ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ሠራተኞች ፍተሻ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ነው የተነገረው፡፡ በቁጥጥ ሥር የዋለውም ሚያዝያ 17 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 7፡00 አካባቢ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘም ብርሃኑ ይመር እና ጣዕመ ገብረመስቀል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ ከጅግጅጋ 150 ኪ.ሜ ርቀት በምትገነው ሀርሸን ወረዳ ጠረፍ ላይ ግምቱ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የግንባታ ግብዓት እና ሌሎች የኮንትሮባድ ዕቃዎች ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በሶማሌ ክልል ሚሊሻ፣ አድማ ብተና፣ በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ ሠራተኞች አማካኝነት ተይዟል፡፡ በክትትል ወቅትም የኮንትሮባድ ዕቃውን የጫነው ተሸከርካሪ የመገልበጥ አደጋ እንደደረሰበት ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- የገቢዎች ሚኒስቴር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *