⬆️ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድአሚን ጀማል ከኃላፊነታው ለመነሳት መልቀቂያ አቀረቡ።

⬆️
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሙሐመድአሚን ጀማል ከኃላፊነታው ለመነሳት መልቀቂያ አቀረቡ። ፕሬዝዳንቱ መልቀቂያውን ያቀረቡት ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት እያካሄደ ባለው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳስታወቀው ፕሬዝዳንቱ በጤና እክል ምክንያት ከኃላፊነት ለመልቀቅ መወሰናቸውን አመልክተዋል፡፡ የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሐጂ ሙሐመድአሚን መልቀቂያ ያቅርቡ እንጂ የምክር ቤቱ ጉባኤተኛ እስካሁን በመልቀቂያው ላይ ውሳኔ እንዳላሳለፈም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *