የተበላሹ መድኃኒቶች ።

EthioNewsflash News Update

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ኤክስትራ ፍሬሽ/Extra fresh/ እና ናቹራል/Natural/ የጥርስ ማጠቢያ በሚል መጠሪያ የተዘጋጁ ፈሳሾች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ያሳስባል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከስር በምዕስሉ ላይ የምትመለከቷቸውን ኤክስትራ ፍሬሽ/Extra fresh/ እና ናቹራል/Natural/ የጥርስ ማጠቢያ በሚል መጠሪያ የተዘጋጁ ፈሳሾች በአዲስ አበባ ከተማ ሀያት አደባይ ፣መገናኛ አደባባይ እና በፒያሳ በተዘጋጁ ባዛሮች ላይ በተደረገ የጤና ቁጥጥር ወቅት መገኘታቸው እየገለጽን፤የምርቶቹ አምራቾቻቸው ስምና አድራሻ የማይታወቁ ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረቱሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀም የባለስልጣን መስሪያቤቱ ያሳስባል፡፡

በማከፋፈልና በሽያጭ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦችና ምርቱ በየካ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በቀጣይ የምርቱን ምንጭ በማጣራት ተጨማሪ እርምጃ እንደሚወስድ እንገልጿል፡፡

ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ ወይም ባዛሮች እንዲሁም የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ ፣ለፖሊስ አካላት ወይም በፌደራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም እንድታሳውቁ እየጠየቅን፡፡የችግሩን አሳሳቢነት ከግንዛቤ በማስገባት ሁሉም አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ይጠይቃል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *