በጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሞቱ ጉማሬዎ ቁጥር 33 ደረሰ።

⬆️
በጊቤ ሸለቆ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ የሞቱ ጉማሬዎች ቁጥር 33 ደረሰ!

ለአንድ ሳምንት ገደማ በቆየ ተከታታይ አሰሳ እስካሳለፍነው እሁድ ድረስ 28 ጉማሬዎች በተመሳሳይ ሁኔታ እየሞቱ መገኘታቸው ይታወቃል። በትናንት እለት ሁለት እና ዛሬም ተጨማሪ ሶስት ጉማሬዎች ሞተው መገኘታቸውን የፓርክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ ባህሯ ሜጋ ነግረውናል።

ትናንት ሞተው ከተገኙት ውስጥ አንዱ በጥይት ተመትቶ መገደሉ የታወቀ ሲሆን ሌሎቹ ከቀደሙት አሟሟት ጋር ተመሳሳይነት ባለው መንገድ ሞተው መገኘታቸውን ነግረውናል።

ቀደም ሲል የሞቱትን ጉማሬዎች አሟሟት የሚያጠና ቡድን ከስፍራው ናሙናዎችን ወስዶ የተመለሰ ሲሆን የናሙና ውጤቱን ይፋ ለማድረግ የአንድ ሳምንት ጊዜ እንደሚያስፈልግ ተገልጧል።

ከዚህ በተጨማሪ ፓርኩ በህገ-ወጥ ሰፋሪዎች መወረር መቀጠሉን የነገሩን ኃላፊዋ ፓርኩ ከመቸውም በላይ አደጋ ላይ እንደሆነ ልብ ሊባል እንደሚገባ ገልጠዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *