ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ 200,000 ሺህ ብር የሚያወጣና ለካንሰር ህሙማን የመድሀኒት መበጥበጫ የሚያገለግል (ሁድ) ለማበርከት ቃል ገባ።

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ 200,000 ሺህ ብር የሚያወጣና ለካንሰር ህሙማን የመድሀኒት መበጥበጫ የሚያገለግል (ሁድ) ለማበርከት ቃል ገባ።

በተጨማሪም ጎሳዬ ከካንሰር ህሙማን ጋ ምሳ ተመግቧል።ከፍለው ለመታከም አቅም ያነሳቸውን የተወሰኑ ህሙማንም ለማሳከም ቃል ገብቷል።

ሲያምሽ ያመኛል የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ የሚገኘው ጎሳዬ ተስፋዬ ዛሬ በምሳ ሰአት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሳይንስ ኮሌጅ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ልዩ የካንሰር ህክምና ማዕከል ከባለቤቱ ወ/ሮ ገነት እና ከሀበሻ ዊክሊ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አዶኒክ ወርቁ ጋ በመሆን ምሳ የማብላት፣ታካሚዎችን የመጠየቅና የማበረታታት መርሀ ግብር አካሂዷል።

ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ከባለቤቱ ወ/ሮ ገነት ተስፋዬ በበጎ አድራጎት ተግባራት ላይ በመሳተፍና ሙያዊ አበርክቶ በማድረግ ከዚህ ቀደም በመሳተፍ የሚታወቅ ሲሆን ከልዩ ማእከሉ ጋ በቀጣይ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግና በድጋፉ ለመቀጠልም ቃል ገብቷል።
ልዩ የካንሰር ህሙማን ማዕከሉ በሀገራችን ብቸኛው ማእከል ሲሆን በቀ ከ60 እስከ 80 ተመላላሽ ታካሚዎችን እንዲሁም 16 የህጻናት እና ሀያ አራት የአዋቂዎች አልጋ አለው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *