ትልቁ ቤተመፃህፍት።

በመሀበራዊ ድህረ ገጽ ላይ የአ.አ ከተማ አስተዳደር Mayor Office of Addis Ababa በሚል ፌስቡክ ገጹ ላይ “በአ.አ ከተማ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ለሀገራችን የመጀመሪያ የሆነ ግዙፍ ቤተ-መጽሀፍ” ሊያስገነባ እንደሆነ አስነብቦናል እንደመረጃው ከሆነ ይህ በሁለት አመታት ውስጥ ተገንብቶ አገልግሎት እንደሚሰጥ የተነገረለት ቤተ-መጽሀፍ
“• ግንባታው አራት ኪሎ ከፓርላማ ፊትለፊት ከአርበኞች ህንፃ ጎን የሚገነባ ይሆናል
• ማዕከሉ 38,687 ካሬ ሜትር ላይ ያርፋል
• በአንድ ጊዜ 3,500 ሰው የሚያስጠቅም እና በቀን እስከ 10,000 ሰው የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል
• ለህፃናት እና አዋቂዎች የሚሆን ለየብቻ የማንበቢያ እና የአረንጓዴ ስፍራ ፤ ከ100 ሰው በላይ የመያዝ አቅም ያላቸው ሶስት የስብሰባ አዳራሾች አሉት
• ለደራሲያን ፣ ከያኒያን እና የጥበብ ሰዎች የሚሆን የመለማመጃ እና የቴአትር ማዕከላት
• ከ130 በላይ መኪኖችን የሚያቆም ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ይኖሩታል” ይላል።
በመረጃው ላይ ይህ ለሀገራችን ግዙፍ የሆነ ቤተ-መጽሀፍ ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚፈጅ ያልተገለፀ ቢሆንም ሀሳቡ ግን ለትውልድ የሚተርፍ ትልቅ የሆነ የዕውቀት ቤት ለመገንባት ነውና ሁላችንም ይበል ልንለው ይገባል!! በነገራችን ላይ ስነ ቤተ-መጽሀፍ ስናወራ የአለማችን ትልቁ ቤተ-መጽሀፍ ማን እንደሆነ ያውቃሉ?????
The Library of Congress ይባላል መገኛውም በዩ ኤስ አሜሪካ መናገሻ ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ ይገኛል ይህ እጅግ በጣም ግዙፍ የሆነ ቤተ-መጽሀፍ በውስጡ 167 ሚልዮን ፋይሎች ሲኖሩት ከዛ ውስጥ በ 450 ቋንቋዎች የተጻፉ

  • ከ39 ሚ..በላይ መጽሀፎች እና የተለያዩ የህትመት ውጤቶች
  • 3.6 ሚ..የተለያዩ የድምጽ ቅጂዎች
  • 14.8 ሚ..ፎቶግራፎች
  • 5.5 ሚ..ካርታዎች
  • 8.1 ሚ.. ሙዚቃዎች
  • 72 ሚ.. ለህትመት ያልበቁ መጽሀፎች ይገኙበታል።
    በዓመት ከ2 ሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት በሚሰጠው በዚህ እጅግ በጣም ግዙፍ በሆነ ቤተ-መጽሀፍ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የመጽሀፍ መደርደሪያዎች አንድ ላይ ቀጥ ተደርገው ቢደረደሩ 1,349 ኪሎ ሚትር እርዝማኔ እንደሚኖራቸው ይነገራል! አጀብ ነው!
    ምንጭ_Interesting facts about the Library of Congress
    googel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *