ክስ የተመሰረተባቸው ቲቪ ጣቢያዎች!!!

ሁለት የቴሌቭዥን ጣቢያዎች የተሳሳተ ማስታወቂያ በማሰራጨት በሚል ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲከፍሉ ተፈረደባቸው፡፡
የማስታወቂያና የብሮድካስት ህጉን በመተላለፍ ሸማቹ እንዲታለል አድርገዋል በሚል 22 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ የተፈረደባቸው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) እና ኢቢኤስ ናቸው፡፡
የሲኖ ትራክ መኪና በግማሽ የቅድሚያ ክፍያ ከውጭ አስመጣላችኋለሁ በሚል በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ሰብስቦ ተሰውሯል የተባለው ዙና ትሬዲንግ ባለፈው ሐምሌ ወር ያላግባብ የሰበሰበውን 58 ሚሊዮን ብር ለ98 ከሳሾች እንዲመልስ እንደተወሰነበት ይታወሳል፡፡
በጉዳዩ ሁለተኛ ተከሳሽ የሆኑት ኢቢኤስና ኢቢሲ ደግሞ ሀሰተኛ ማስታወቂያ በማሰራጨታቸው ሀላፊ ተደርገው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 6ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ከትናንት በስትያ ባስቻለው ችሎት ከ58 ሚሊዮን ብሩ 1/4ኛውንና የተለያዩ ወጭና ማካካሻዎችን ጨምሮ ወይንም ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ በድምሩ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡
በጊዜው በቴሌቪዥን ጣቢየዎች የተሰራጨው የዙና ትሬዲንግ ማስታወቂያ ከውጭ ያስመጣቸው መኪኖች እንዳሉት የሚናገርና መኪኖች ተደርድረው በምስል የሚታዩበት ነበር፡፡
ይሁንና ድርጅቱ አንድም መኪና ከውጭ አለማስገባቱ በመረጋገጡ በሀሰተኛ ማስታወቂያ ህብረተሰቡ እንዲያምነውና ዙና ትሬዲንግ ያላግባብ 58 ሚሊዮን ብር እንዲሰበሰብ ምክንያት ሆነዋል በሚል የሚድያ ተቋማቱ ባሰራጩት ማስታወቂያ ፍርድ ቤቱ ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡




በመሆኑም ኢቢሲና ኢቢኤስ የማስታወቂያና የብሮድካስት ህጉን በመተላለፋቸው፣ በአሳሳች ማስታወቂያ ሸማቾች እንዲታለሉ በማድረግ ከውል ውጭ ያለ ሀላፊነት መሰረት በማድግ በቀረበባቸው ክስ የዋናውን ክስ 1/4ኛ ወይንም ከ22 ሚሊየን ብር በላይ ባልተነጣጠለ ሀላፊነት እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል፡፡
በማስታወቂያ ህጉ መሰረት ማስታወቂያ እየተሰራለት ለእይታ የሚበቃው ቁስ በህጋዊ መንገድ ስለመገዛቱና የኢትዮጵያን ደረጃ የሚያሟላ ስለመሆኑ ማረጋገጥም የማስታወቂያ ሰሪውና አሰራጭው ሀላፊነት ነው፡፡
(ትዕግሰት ዘሪሁን)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *