መረጃ አዲስ አበባ።

ፖሊስ የአዲስ አበባ ባለ-አደራ ደጋፊዎች የተለያዩ የከተማው ቦታዎች የሰቀሉትን ባነሮች ከደንብ አስከባሪዎች ጋር በመሆን እያወረደ መሆኑ ታውቋል። በሌላ ዜና በዶሮ ማነቂያ አካባቢ በስራ ላይ የሚገኙ ሁለት ግለሰቦችን ባነር የሰቀላችሁት እናተ ናችሁ በማለት በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል። ባነሩ የተሰቀለበት ፖል አጠገብ የግሮሰሪ ባለቤት የሆኑት አቶ ሲሳይ የተባለ ግለሰብ እና በአካባቢው ላይ በልብስ ስፌት የሚተዳደር አቶ ደምስ የተባለ ግለሰቦች በፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ውለዋል።


በአሁኑ ሰአትም ሁለቱም ግለሰቦች ጣይቱ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።
ጋዜጠኛ እሰክንድር ነጋም በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ከሚመለከታቸው የጣቢያው ኃላፊዎች ጋር ለመነጋገር በፖሊስ ጣቢያው ተገኝቷል። ጉዳዩ የሚመለከተው የጣቢያው አዛዥ ነው በሚል ከጣቢያው አዛዥ ጋር ለመነጋገር ጋዜጠኛ እስክንድር በፖሊስ ጣቢያው በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

ፎቶ: አቶ ሲሳይ በጣይቱ ፖሊስ ጣቢያ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *