ኩላሊታችን የቱ ጋር ነው?

የኩላሊት ህመም ወይም መድከም ዛሬ አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ላይ በሽታ ይስተዋላል።
ብዙዎች የኩላሊት ህመምን እንደቀላል በማየት ብርድ ነው፣ጨጓራ ነው፣ ወገቤን ነው በማለት የቀኝና የግራ ኩላሊት
በየት አካባቢ የሰውነት ክፍላችን እንደሚቀመጥ ለማሳየት ነው።
ህመም ሲሰማን በማስታገሻ ሰውነታችንን ማለማመድ ለኩላሊት መድከም ዋነኛ ተጠቃሽ ነው።
በተለይ አመጋገባችን ለጤንነታችን ሰፊ ድርሻ አለው 
ለምሳሌ ,,,የታሸጉ ምግቦች
በየቀኑ ስጋና ቅባት ምግቦችን ማዘውተር።
የፖልም ዘይት መጠቀም
ሌላው በመኝታ ሰዓት መመገብና እንቅስቃሴ ሳናደግ መተኛት ለከፍተኛ ጉዳት ይዳርጋል።

በመጠጥ ደረጃ አልኮል መጠጦችን ቅባትነት ያላቸው ውስኪ የመሳሰሉ መጠጦች ለበሽታው ተጋላጭ ያደርጋል።

ጣፋጭ ለስላሳ መጠጦችም ከፍተኛ ስኳርነት ስላላቸው 
አይመከሩም ሁሉንም በልክና አልፎ አልፎ መጠቀሙ ይመከራል።

#ኩላሊት #ሲጎዳ #የሚታዩ 8 #ምልክቶች

1. ኩላሊታችን ችግር ሲያጋጥመው የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ ትንፋሽ ሊያሳጥረን ይችላል

2. ምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም መሰማት – የኩላሊት ችግርን ተከትሎ በደም ውስጥ የንጥረ ነገሮች ይዘት ላይ ለውጥ ስለሚኖር በምላሳችን ላይ የብረት ጣዕም ከመሰማት ጀምሮ እስከ ጠቅላላ የምግብ ጣዕም ለውጥ ሊኖር ይችላል፡፡ የደም ይዘት ለውጥን ተከትሎ የምግብ ፍላጎት መቀነስ ችግርም ያጋጥማል፡፡

3. የውሃ ሽንት ቀለም ለውጥ – የሽንት ከለር ለውጥ አንዱ የኩላሊት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይም የውሃ ሽንት ከለር ጠቆር ወዳለ ብጫ ከለር በተደጋጋሚ ከተስተዋለ የኩላሊት ጉዳት ውጤት ሊሆን ይችላል፡፡

4. የትኩረት መቀነስ – የኩላሊት መጎዳት ኦክሲጅን በአግባቡ ወደ ጭንቅላት እንዳይሄድ ስለሚያደርግ የማስታወስ ችግርና የትኩረት ማጣትን ያስከትላል፡፡

5. የሰውነት አካል እብጠት – የኩላሊት ጉዳት በሰውነታችን የሚገኙ ፈሳሾች በአግባቡ እንዳይወገዱ ስለሚያደርግ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል፡፡ በተለይም እግር ፣ መገጣጠሚያና ፊት ላይ እብጠት ሊከሰት ይችላል፡፡

6. የሰውነት መዛል – የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ የቀይ ደም ህዋስ ቁጥር ስለሚቀንስ የሰውነት ማዛልን ጨምሮ የአዕይምሮና የጡንቻዎች ችግር ሊያጋጥም ይችላል፡፡

7. የቆዳ አለርጂ – የኩላሊት ጉዳትን ተከትሎ በሰውነታችን የመርዛማ ንጥረ ነገሮች ክምችት ስለሚጨምር የቆዳ አለርጂ ሊያጋጥም ይችላል፡፡

8. የኩላሊት አካባቢ ህመም የኩላሊት ኢንፌክሽን ኩላሊት አካባቢ ህመም እንዲሰማ ያደርጋል፡፡

ከላይ የተጠቀሱ ምልክቶች የኩላሊት ጉዳት ችግር ሊሆን ስለሚችል ኩላሊቶን በመመርመር ሊታደጉት ይገባል ይላል የናሽናል ኪድኒ ፋውንዴሽን መረጃ

በማድረግ ብዙዎችን ከጉዳት እንታደግ::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *