የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተዋሃዱ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2011

የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተዋሃዱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 9፣ 2011 የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመዋሃድ የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

ፓርቲዎቹ ዛሬ በመሪዎቻቸው በኩል ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

የተባበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመወከል አቶ ገላሳ ዲልቦ እና የሽግግር ኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በመወከል ደግሞ አባነጋ ጃራ ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

ፓርቲዎቹ ለህዝቡ ሰላም እና አንድነት በጋራ ለመስራትም በማስብ መዋሃደችውን ነው ያመለከቱት።

መላው የኦሮሞ ህዝብ እና ለኦሮሞ ህዝብ የሚታገሉ ሀይሎች የመጣውን ለውጥ ወደፊት ለማስኬድ ድጋፍ እንዲያደርጉ ብሎም በጋራ ተሰባስበው እንዲሰሩ ጥሪ አቅበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *